ቀጥታ፡

ከክልሉ ባለፉት ሥድስት ወራት 270 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ቀረበ

ቦንጋ፤ ጥር 19/2018 (ኢዜአ)፡- በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ 270 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ወልያብ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበውን የወርቅ ምርት ለማሳደግ እየተሠራ ነው።

ለአብነትም በአንድ ወረዳ ብቻ ይመረት የነበረውን ወደ አራት ወረዳዎች ማስፋት መቻሉ እና የአምራች ማኅበራት ቁጥር መጨመሩንም ገልጸዋል።

በወርቅ ግብይቱ ይስተዋሉ የነበሩ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል ግብይቱ በተደራጁ ማዕከላት እንዲከናወን መደረጉንና የቁጥጥር ሥራውም መጠናከሩን አመላክተዋል።

በሌላ በኩል ለ142 ማኅበራትና ከ15 ለሚልቁ ወርቅ አቅራቢዎች አዲስ ፈቃድ መሰጠቱን ገልፀዋል።
 
እንዲሁም 90 ሺህ ቶን የድንጋይ ከሰል መመረቱን ነው ያመላከቱት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም