ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር መርሐ-ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የካቲት 7 ቀን 2018 . 14 ሳምንት መርሐ-ግብር ይጀመራል።


 

14 ሳምንት ጨዋታዎች ከየካቲት 7 እስከ 9 ቀን 2018 . ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የካቲት 7 ይጀመራል

በዚህም የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ነው።


 

ኢትዮ ኤሌክትሪክ 36 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዟል። መቻል 29 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሸገር ከተማ ይጫወታል።


 

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 32 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ 27 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

በሌሎች 14 ሳምንት መርሐ-ግብሮች ሐዋሳ ከተማ ከአዳማ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከሲዳማ ቡና፣ ይርጋጨፌ ቡና ከአርባምንጭ ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማ ከባህርዳር ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ከልደታ ክፍለ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር መርሐ-ግብር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚደረግ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም