የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ
ሐረር፤ ጥር 19/2018 (ኢዜአ)፡- የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ ስድስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።
ለአንድ ቀን የሚካሄደው ጉባዔው፤ የስድስተኛ ዙር አራተኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ የ2018 የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ የሚጸድቅ ይሆናል።
ጉባዔው የሐረሪ ብሔረሰብ ቋንቋና ባህልን በሚመለከት ፖሊሲና ሕግን ጨምሮ የቅርስ አጠባበቅ መመሪያ የሚያወጣ ሲሆን፤ 14 መቀመጫዎችም አሉት።