ቀጥታ፡

የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶቹ የኢትዮጵያን የሩቅ ዘመን የልዕልና ህልም በተጨባጭ በቅርቡ እንደምናሳካው ማረጋገጫዎች ናቸው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ)፦ በአየር ኃይል ኤክስፖው የታዩ የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢትዮጵያን የሩቅ ዘመን የልዕልና ህልም በተጨባጭ በቅርቡ እንደምናሳካው ማረጋገጫዎች ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዓለም አቀፍ የአየር ኃይል ኤክስፖን ዛሬ ጎብኝተዋል።


 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የ90 ዓመታት ጉዞ በድልና በጀግንነት ብቻ የተገደበ አይደለም፤ በፈጠራና የቴክኖሎጂ ልዕልና ውጤትም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።

በአየር ኃይል ዋና መሥሪያ ቤት በተከፈተው ዓለም አቀፍ የአየር ኃይል ኤክስፖ ዛሬ የተመለከትነው እውነትም ይሄንኑ የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።


 

በኤክስፖው የተመለከትናቸው የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢትዮጵያን የሩቅ ዘመን የልዕልና ህልም በተጨባጭ በቅርቡ እንደምናሳካው ማረጋገጫዎች ናቸው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም