ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ተደርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23 ነጥብ 8ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ምድረ ገነት ሽሬ በ21 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ ተከታታይ የሊግ ድል የማስመዝገብ ፍላጎት አልተሳካም።