ባህር ዳር እና ሃዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር እና ሃዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሐ - ግብር ባህር ዳር እና ሐዋሳ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተካሄዷል።
ባህር ዳር ከተማ በ22 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል።
ሐዋሳ ከተማ በ29 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ፋሲል ከነማ አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ቃልኪዳን ዘላለም ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ቀሪዋን ጎል ለፋሲል ከነማ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ታምራት እያሱ በጨዋታ እና ፀጋዬ አበራ በፍጹም ቅጣት ምት ለአርባምንጭ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ከሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል የተመለሰው ፋሲል ከነማ በ29 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። በሊጉ ሰባተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።
አርባምንጭ ከተማ በሊጉ ምንም ድል ያላስመዘገበ ብቸኛው ቡድን ነው።
አዳማ ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ቀን ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ የመጀመሪያ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።