ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፤ ጥር 17 /2018 (ኢዜአ)፡- የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዛሬ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ይደረጋል።

ውድድሩ ለክልል፣ ከተማ አስተዳደር፣ ክለብ፣ ተቋማትና የግል ተወዳዳሪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ያለመ ነው።



በውድድሩ ላይ 109 ወንዶች እና 64 ሴቶች አትሌቶች እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።

ፌደሬሽኑ የአሸናፊዎችን ሽልማት 366 ሺህ ብር ጨምሮ ለውድድሩ ማስኬጃ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ማዘጋጀቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም