ቀጥታ፡

ቦርንማውዝ ሊቨርፑልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥር 16 /2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታ ቦርንማውዝ ሊቨርፑልን 3 ለ 2 አሸንፏል።

ማምሻውን በቫይታሊቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢቫኒልሰን፣ አሌክስ ሂሜኔዝ እና አሚን አድሊ ለቦርንማውዝ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።



አሚን አድሊ 95ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ግብ ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።

ቨርጅል ቫን ዳይክ እና ዶምኒክ ስቦዝላይ ለሊቨርፑል ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።




ለቦርንማውዝ ግቦች መቆጠር የተከላካይ ክፍሉ በተለይም የሊቨርፑሉ ቨርጅል ቫን ዳይክ ስህተቶች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው።

ጨዋታው አዝናኝ እንቅስቃሴ ተደርጎበታል።

በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቦርንማውዝ በ30 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊቨርፑል በ36 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።



የቀያዮቹ በሊጉ ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ተገቷል። በሁሉም ውድድሮች ከ13 ጨዋታዎች በኋላ የመጀመሪያ ሽንፈት አስተናግደዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም