የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱን ተርሚናል ዛሬ ጎብኝተዋል።
በዚህም፥ ተርሚናሉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ፣ለተሳፋሪዎች ተመቻችቶ፤ ለዕይታ ተስማምቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆንም ጠቁመዋል።