ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ትብብራቸውን ለማጠናከር ያለመ ምክክር አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ትብብር በይበልጥ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት አግባብ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከፎረሙ ፕሬዚዳንት ቦርጌ ብሬንድ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተካሄደው በዳቮስ ከተካሄደው የ2026 የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ጎን ለጎን ነው።


 

በውይይቱ ወቅትም ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፤ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ ለፕሬዚዳንቱ ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ አጋሮች ጋር በዓለም አቀፍ ልማት፣ ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ ላይ እንድትመክር ፎረሙ ላበረከተው መልካም አጋጣሚም አመሥግነዋል።

በቀጣይም ሁለቱ ወገኖች ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በልማት አጋርነት ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ የላከው መረጃ አመላክቷል።


 

ኢትዮጵያ በ2026 የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ያደረገችው ተሳትፎ በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም