የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ተጠቃሚነት እያሳደገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ተጠቃሚነት እያሳደገ ነው
አሶሳ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ችግር በማቃለል የተረጋጋ ኑሮ እንዲመሩ ማስቻሉን የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ደን ልማት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቡራሞ ወረዳ ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ለዐቅመ ደካሞች አስረክቧል።
በዚሁ ወቅት አቶ ከበደ፤ ለዐቅመ ደካሞች የሚደረገው ድጋፍ መንግሥት ለወገን ደራሽ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ብሎም እያከናወነ ያለው ሰው ተኮር ተግባር አካል ነው ብለዋል።
ከቤት ግንባታ በጨተማሪ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአካባቢው ማኅበረሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል።
የቤቱ ባለቤቶች ፈዳይል ደኑ እና ኪፈያ አሲመድ በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊት የነበረው የመኖሪያ ቤታቸው ለመኖሪያ ምቹ እንዳልነበረ አውስተዋል።
አሁን የኢትዮጵያ ደን ልማት ምቹ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ ስለሰጣቸው መደሰታቸውን እና ቤቶቹ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ሙሉ የቤት ዕቃ የተሟላላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
መንግሥት እያከናወነ ያለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።