የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ታውቀዋል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ታውቀዋል
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ እጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሄዷል።
በዚሁ መሠረት ነገሌ አርሲ ከሲዳማ ቡና፣ ቤንች ማጂ ቡና ከኢትዮጵያ መድን፣ መቻል ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ቦዲቲ ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ በሩብ ፍጻሜው ይጫወታሉ።
የሩብ ፍጻሜ መርሐ-ግብር መጋቢት 12 እና 13 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ዋንጫን የሚያሸንፈው ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።
በ1937 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ዋንጫ 81 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ ውድድር ነው።