ከተሞች ቅርስና ጥሪታቸውን ከዘመናዊነት ጋር ሲያዋህዱ የሰላም እና ልማት ምሰሶ ይሆናሉ- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ - ኢዜአ አማርኛ
ከተሞች ቅርስና ጥሪታቸውን ከዘመናዊነት ጋር ሲያዋህዱ የሰላም እና ልማት ምሰሶ ይሆናሉ- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ
አዲስ አበባ፤ጥር 15/2018 (ኢዜአ)፡-ከተሞች ቅርስና ጥሪታቸውን ከዘመናዊነት ጋር ሲያዋህዱና ሲያስማሙ የሰላም እና ልማት ምሰሶ ይሆናሉ ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ።
ፕሬዝዳንት ታዬ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የኢትዮጵያ የከተሜነት ጉዞ እየተገለጠ እና ብርቱ እንደሆነ ትልሙን ፣ ተግባሩንና ቀጣይ መዳረሻውን እየተመለከትን ነው ብለዋል።
ከተሞች ቅርስና ጥሪታቸውን ከዘመናዊነት ጋር ሲያዋህዱና ሲያስማሙ የዕውቀት፣ የሥራ፣ የልማት፣ የሰላም አምባና መቅረዝ ይሆናሉ ሲሉ ገልጸዋል።