ቀጥታ፡

የኮሪደር ልማት የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አነቃቅቷል

ወልዲያ፤ ጥር 15/2018(ኢዜአ)፦ በወልዲያ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት አማራጭ የመዝናኛ ቦታዎችን ከመፍጠር ባለፈ የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያነቃቃ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ።

ዕድሜ ጠገቧ የወልዲያ ከተማ በኮሪደር ልማቱ ውብና አዲስ ገጽታን ተላብሳለች።


 

ከተማዋ ያላትን ጸጋ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለመቀየርና የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል እያበረከተ ያለው ሚና የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ነዋሪዎች መካከል አለበል እሸቱ፣ የኮሪደር ልማቱ በተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች የተገነቡ የንግድ ሱቆች የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አነቃቅተዋል ብለዋል።


 

የኮሪደር ልማቱ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረገ አማራጭ የመዝናኛ ቦታዎችን መፍጠሩን የተናገሩት ደግሞ ያለው አሰፋ ናቸው። 

ልማቱ በጥራትና በፍጥነት መከናወኑንም አንስተዋል።

የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ በበኩላቸው፣ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ በበጎ ከመቀየር ባለፈ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ አዎንታዊ ሚና ማሳደሩን ተናግረዋል።


 

ከኮሪደር ልማቱ ፈጠራና ፍጥነትን ታሳቢ በማድረግ በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወነ መሆኑንም አንስተዋል።

በከተማዋ ባለፈው አንድ ዓመት 2  ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት መጠናቀቁን ጠቅሰው፣ ቀሪው የ2 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ኮሪደር ልማት በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በወልዲያ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ከ550 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ለዕውቀት ሽግግር ከፍተኛ ጠቀሜታ እያበረከተ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም