የአቪዬሽን ኤክስፖው የኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚናን የሚያጠናክር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የአቪዬሽን ኤክስፖው የኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚናን የሚያጠናክር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2018(ኢዜአ)፦ የአቪዬሽን ኤክስፖው የኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚናን እንደሚያጠናክር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን በማስመልከት በተሰናዳው የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 መክፈቻ ላይ መገኘታቸውን ጠቁመዋል።
የአቪዬሽን ኤክስፖው “ወደፊት መብረር፣ የጋራ ነገን መገንባት” በሚል መሪ ቃል መዘጋጀቱን አመልክተዋል።
ኤክስፖው የአቪዬሽን ቴክኖሎጂን፣ ክህሎትን፣ ትብብርን የማሳደግና በማደግ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚናን ለማጠናከር የሐገር ውስጥ እና የውጭ ተባባሪ አካላትን በአንድ መድረክ ያገናኘ መሆኑን ተናግረዋል።