ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀው የአቪዬሽን ኤክስፖ መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል

አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2018 (ኢዜአ)፦‎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተሰናዳው የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 ይፋዊ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል።


 

‎ኤክስፖው “የወደፊቱን የአቬሽን አቅም በጋራ እንገባ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።


 

ኤክስፖው ኢትዮጵያ ለአቪዬሽን እና ኤሮስፔስ ልማት፣ አለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር እና ሀገራችንን በአቪዬሽን ልማት የቀጣናው እና አኅጉሩ የፈጠራ፣ የክህሎት ልማት እና የዘላቂ እድገት ማዕከል ማድረግ ላይ ያላትን ጽኑ አቋም እና ተግባር የሚያሳይ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም