ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ የታየው የልማት ሥራ የሚደነቅ ነው - የአፋሕድ አመራሮች

አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ የታየው የልማት ሥራ የሚደነቅ ነው ሲሉ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራሮች ገለጹ፡፡

የአፋሕድ ከፍተኛ አመራሮች ማስረሻ ሰጤ እና ፈንታው ሙሀባውን ጨምሮ የድርጅቱ አባላት በመዲናዋ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ በሥፍራው ተገኝተው ጎብኝተዋል።

በዚህም በመዲናዋ የተሰሩ የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።


 

እየተሰራ ያለው ሥራ ስንሰማው ከነበረው በተቃራኒው አስደናቂ ሆኖ አግኝተነዋል ያሉት የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራሮችና አባላት፤ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት በግጭት ውስጥ መቆየቷን ያስታወሱት አመራሮቹ፤ ሰላሟን ለማስጠበቅ እና ልማት ለማረጋገጥ በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል መንግሥትና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) መካከል የተደረሰውን ዘላቂ የሰላም ስምምነት ውጤታማ የሚያደርግ ስምምነት በትናንትናው ዕለት መፈረሙ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም