የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በመጋቢት ወር ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በመጋቢት ወር ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2018 (ኢዜአ)፦ የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ-ግብር በመጋቢት ወር 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የሩብ ፍጻሜ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ነገ ማለዳ እንደሚካሄድ አመልክቷል።
ሲዳማ ቡና፣ መቻል፣ ኢትዮጵያ መድን፣ መቀሌ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ነገሌ አርሲ፣ ቤንች ማጂ ቡና እና ቦዲቲ ከተማ ለሩብ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ናቸው።
የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ወላይታ ድቻ በሁለተኛው ዙር መሰናበቱ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ዋንጫን የሚያሸንፈው ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።
በ1937 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ዋንጫ 81 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ ውድድር ነው።