ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፤ ጥር 14/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብለስ ናጎ፣ ፍራኦል መንግስቱ እና ዮሴፍ ዮሐንስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሲዳማ ቡና በ33 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። በሊጉ ዘጠነኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በ19 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ-ግብር መቻል ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ፈቱዲን ጀማል የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ26 ነጥብ ደረጃውን ከ7ኛ ወደ 3ኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ22 ነጥብ ከነበረበት 8ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ዝቅ ብሏል።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ16ኛ ሳምንት መርሐ- ግብር ተጠናቋል።
የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።