ቀጥታ፡

ባየር ሙኒክ በሻምፒዮንስ ሊጉ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2018(ኢዜአ)፦  በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሐ-ግብር ባየር ሙኒክ ዩኒየን ሴይንት ጂልዋን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሃሪ ኬን በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሃሪ ኬን በሻምፒዮንስ ሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ ሰባት አድርሷል። በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድሮች ያገባቸውን ግቦች ወደ 34 ከፍ አድርጓል።

የባየር ሙኒኩ ሚን-ጄ ኪም በ63ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ባየር ሙኒክ በ18 ነጥብ ከአርሰናል በመቀጠል ጥሎ ማለፍ የገባ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል። በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ ይገኛል።

የቤልጂየሙ ዩኒየን ሴይንት ጊልዋ በስድስት ነጥብ 31ኛ ደረጃን ይዟል።

በሌሎች ጨዋታዎች ሊቨርፑል ማርሴይን 3 ለ 0 አሸንፏል። ዶምኒክ ስቦዝላይ፣ ኮዲ ጋፕኮ እና የማርሴይ ግብ ጠባቂ ጄሮኒሞ ሩሊ በራሱ ላይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሊቨርፑል በ15 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ማርሴይ በዘጠኝ ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቼልሲ ፓፎስን በሞሰስ ኬይስዶ ግብ 1 ለ 0 ረቷል።

ባርሴሎና ከሜዳው ውጪ ስላቪያ ፕራግን 4 ለ 2 አሸንፏል። ፌርሚን ሎፔዝ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ዳኒ ኦልሞ እና ሮበርት ሌዋንዶስኪ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ቫሲል ኩሴጅ እና የባርሴሎና ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በራሱ ላይ ለስላቪያ ፕራግ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በአሮን ዊሳ፣ አንቶኒ ጎርደን እና ሃርቪ ባርንስ ግቦች ፒኤስቪ አይንድሆቨንን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ጁቬንቱስ ቤኔፊካን 2 ለ 0፣ አትሌቲኮ ቢልባኦ አትላንታን 3 ለ 2 አሸንፈዋል።

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ መርሐ-ግብር በቀጣይ ሳምንት ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም