ቀጥታ፡

ጋላታሳራይ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2018(ኢዜአ)፦‎ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሰባተኛ ዙር መርሐ ግብር ጋላታሳራይ እና አትሌቲኮ ማድሪድ አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

ማምሻውን በራምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጁሊያን ሲሚዮኒ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ የስፔኑ ቡድን መሪ ሆኗል። 

የአትሌቲኮ ማድሪዱ ተከላካይ ማርኮስ ሊዮሬንቴ በ20ኛው ደቂቃ ላይ በራሱ ላይ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ጋላታሳራይን አቻ አድርጓል። 

በጨዋታው ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ በወሰደው ብልጫ ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር አልቻለም።

ውጤቱን ተከትሎ ጋላታሳራይ በ10 ነጥብ 16ኛ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ በ13 ነጥብ 8ኛ ደረጃን ይዘዋል። 


 

ማምሻውን በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ካራባግ ኢንትራክት ፍራንክፈርትን 3 ለ 2 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም