አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል እንድትሆን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል እንድትሆን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2018(ኢዜአ)፦አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሁም የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረጉን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በአዘርባጃን ባኩ ከተማ በሚካሄደው የዓለም ከተሞች ፎረም ላይ አዲስ አበባ ያላትን ተሞክሮ የምታካፍልበትን ሁኔታ አስመልክቶ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ እና የዩ ኤን ሀቢታት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ኦውማር ሲላ ጋር ዛሬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
መድረኩ አዲስ አበባ በዘርፉ ልምዷን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የምታካፍልበት እና ተሳትፎዋን ይበልጡኑን የምታሳድግበት ትልቅ አጋጣሚ እንደሚሆን ገልጸዋል።
አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሁም የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረጉን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አመላክተዋል።