በተጠባቂው ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ነገሌ አርሲን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ነገሌ አርሲን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሃዋሳ ከተማ ነገሌ አርሲን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሽመልስ በቀለ በ12ኛው እና ተባረክ ሄፋሞ በ79ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ28 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ሽንፈት ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ በ26 ነጥብ ከነበረበት ሁለተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ዝቅ ብሏል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱንም አስተናግዷል።