ቀጥታ፡

ምድረ ገነት ሽሬ ከተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ ድል መንገድ ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ምድረ ገነት ሽሬ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስንታየሁ ወለጬ በአምስተኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

ከሁለት ሽንፈቶች በኋላ ወደ ድል የተመለሰው ምድረ ገነት ሽሬ በ20 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 10ኛ ከፍ ብሏል።በሊጉ አምስተኛ ድሉን አሳክቷል።

በውድድር ዓመቱን ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።

አርባምንጭ ከተማ በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ ያላስመዘገበ ብቸኛ ቡድን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም