ቀጥታ፡

ወላይታ ድቻ እና ባህር ዳር ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ወላይታ ድቻ እና ባህር ዳር ከተማ ያለ ግብ  አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው የተካሄደው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ነው።

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ14 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ባህር ዳር ከተማ በ21 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። በተከታታይ ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቀሌ 70 እንደርታ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም