ቀጥታ፡

የሐረር ኮሪደር ልማት ለከተራና ጥምቀት በዓል ተጨማሪ ድምቀት ሆኗል

ሐረር፤ ጥር 12/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረር ከተማ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ለከተራና ጥምቀት በዓል ተጨማሪ ድምቀት መስጠቱን የበዓሉ ታዳሚዎች ገለጹ።


 

የበዓሉ ታዳሚ ብሩክ ጥላሁን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ለበዓሉ ተጨማሪ ድምቀት ሰጥቷል።

የተገነቡት ሰፋፊ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለምዕመኑ ማረፊያ፣ ለበዓሉ ድምቀት መስጠታቸውን የተናገሩት ደግሞ ሐብታሙ ተሾመ ናቸው።

አገሬነሽ ገድሉ በበኩላቸው፤ በኮሪደር ልማት የተሠራው መንገድ ቀደም ሲል የነበረውን መጨናነቅ ከማስቀረቱ ባለፈ ለበዓሉ ልዩ ገጽታ እንዳጎናጸፈው ተናግረዋል።


 

በዓሉበድምቀት ማክበራቸውን የገለጹት ሻለቃ አገኘሁ ተክሉማኅበረሰቡ ለአብሮነት ያለውን ቀናነት ማሳየቱን ገልጸው፤ የመደጋገፍ ዕሴትን በማጠናከር ረገድ በጋራ መሥራት ይገባናል ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ለኮሪደር ልማቱ፣ ለበዓሉ ድምቀትና ሰላማዊነት ላበረከተው አስተዋጽዎ አመሥግነዋል።

በዓሉ ሐማኖታዊ እና ባህላዊ ይዘቱን በጠበቀ ሁኔታ በድምቀት መከበሩንም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም