ቀጥታ፡

የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በስኬት ተጠናቅቋል

አዲስ አበባ፣ጥር 11/2018(ኢዜአ) ፦በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከበረው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በመላው ሀገሪቱ በታላቅ ድምቀት የተከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ ‎የፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሰፊ የሰው ኃይል በማሰማራት ተገቢውን የፀጥታ ሥራ በማከናወን ኃላፊነቱን መወጣቱን አስታውቋል።


 

የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ መሠረት በማድረግ የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት በማስቀደም ከከተራ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተጠናከረ ጥበቃ በማከናወን በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።


 

እንዲሁም ለፀጥታና ደኅንነት አካላት አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ ያበረከቱትን የሃይማኖት አባቶች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች፣ የእምነቱ ተከታዮች እና ወጣቶች አመስግኗል።

በነገው ዕለት የሚከበረው ቃና ዘገሊላ በዓልም በስኬት እንዲጠናቀቅ ሕብረተሰቡ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም