የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለጥምቀት በዓል የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለጥምቀት በዓል የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ጥር 11/2018 (ኢዜአ)፦ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ የጥምቀት በዓል ለሚያከብሩ በሙሉ መልካም በዓል ሲል ተመኝቷል።
በዓሉ ሰላም፣ ጤና፣ ደስታ እና ሀሴት ለሁሉም ይዞ የሚመጣበት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የደስታ ይሁንላችሁ ብሏል።
ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆን የተመኘው ደግሞ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ነው።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ የጥምቀት በዓል የደስታ እና የሀሴት እንዲሆን ተመኝቷል።
በኢትዮጵያ የአርሜኒያ ኤምባሲ የጥምቀት በዓል የደስታ እና የበረከት እንዲሆን የተመኘ ሲሆን የካናዳ ኤምባሲ በበኩሉ በዓሉ የደስታ፣የሰላም እና የፌሽታ ይሁን ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
ጀርመን፣ ኔዘርላንድስ፣ ስዊድን፣ ፊንላንድ እና ፓኪስታን ሌሎች ለጥምቀት በዓል መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ኤምባሲዎች ናቸው።
በተያያዘም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ የጥምቀት በዓል የሰላም እና የደስታ እንዲሆን ተመኝቷል።
ጥምቀት እ.አ.አ በ2019 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት/ዩኔስኮ/ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡን አስታውሷል።