ቀጥታ፡

ሳዲዮ ማኔ የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፤ ጥር 10/2018 (ኢዜአ)፦  የሴኔጋሉ ሳዲዮ ማኔ የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሆኗል።

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።

ሴኔጋል አዘጋጇ ሞሮኮን 1 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታለች።

የሴኔጋሉ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።

የሞሮኮው ብራሂም ዲያዝ አምስት ግቦች በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አጠናቋል።

የሞሮኮው ያሲን ቦኖ የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኖ ተመርጧል።

የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አግኝቷል።

በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር)፣ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እና የአዘጋጇ ሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፋውዚ ሌክጃ ተገኝተዋል።

ሞሮኮ የቀጣዩን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነት ለኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛንያ አስረከባለች።

ሶስቱ ሀገራት በጣምራ 36ኛውን የአፍሪካ ዋንጫን እ.አ.አ በ2027 ያዘጋጃሉ።

በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 52 ጨዋታዎች 121 ግቦች የተቆጠረበት ሲሆን በውድድሩ ታሪክ ከፍተኛ የግብ መጠን የተቆጠረበት ሆኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም