ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ኤቨርተን አስቶንቪላን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኤቨርተን አስቶንቪላን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቲዬርኖ ባሪ በ59ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያ ግቡን አስቆጥሯል።

በጨዋታው ላይ አስቶንቪላ ብልጫ ቢወስድም ግብ ማስቆጠር አልቻለም።

ኤቨርተን የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴው አሸናፊ አድርጎታል።

በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ድሉን ያስመዘገበው ኤቨርተን በ32 ነጥብ ከ12ኛ ደረጃ ወደ 10ኛ ከፍ ብሏል።

ኤቨርተን ከ10 ዓመታት በኋላ አስቶንቪላን በሊጉ ማሸነፍ ችሏል።

በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አስቶንቪላ በ43 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

አስቶንቪላ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ የማድረግ እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ዛሬ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ዎልቭስ ከኒውካስትል ዩናይትድ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የ22ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ-ግብር
በብራይተን እና ቦርንማውዝ መካከል ነገ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም