ቀጥታ፡

የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈጥሮን እና የትናንትን ወረት ለነጋችን ብሩኅነት በአንድ ያሰባስባል

አዲስ አበባ፤ ጥር 10/2018 (ኢዜአ)፦‎ የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈጥሮን እና የትናንትን ወረት ለነጋችን ብሩኅነት በአንድ ያሰባስባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ዛሬ ጠዋት በመረቅነው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ይኽን በግልጽ ተመልክተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።


 

ሥራው ከአካባቢው በተገኙ የግንባታ ቁሳቁሶች እና በአካባቢ አቅም የተገነባ በመሆኑ ዘላቂነትን እና ባለቤትነትን ያንፀባርቃልም ነው ያሉት።


 

ኢትዮጵያ ሀገራችን በባሕል፣ በተፈጥሮ እና ታሪካዊ ጥሪቶች የታደለች በመሆኗ ዛሬ ያለንን ጉልበት እና ጥንካሬ ለመጪዎቹ ተከታታይ ትውልዶች በሚተርፍ መንገድ ሀብቶቿን መግለጥ መቀጠል ይኖርብናል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም