ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ አርሰናል እና ኖቲንግሃም ፎረስት አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኖቲንግሃም ፎረስት እና አርሰናል ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ማምሻውን በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ብልጫ ወስዶ የተጫወተው አርሰናል ያገኛቸውን የግብ እድሎች አለመጠቀሙ ሶስት ነጥብ እንዳያገኝ አድርጎታል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ጋብርኤል ማርቲኔሊ የሳተው ግልጽ የግብ እድል ተጠቃሽ ነው።

ተጋጣሚው ኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ኋላ አፈግፍጎ የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት ስልት ይዞ በመግባት ግብ ሳይቆጠርበት ወጥቷል።

ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥቡን ወደ 50 ከፍ አድርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል።

አርሰናል ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ያላሸነፈ ሲሆን ግብም ማስቆጠር አልቻለም።

ኖቲንግሃም ፎረስት በሊጉ በ22 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም