ቀጥታ፡

ናይጄሪያ ግብጽን በማሸነፍ በአፍሪካ ዋንጫው ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፤ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦‎ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ ናይጄሪያ ግብጽን በመለያ ምት አሸንፋለች።

ማምሻውን በመሐመድ አምስተኛ ስታዲየም የተደረገው ጨዋታ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል።

ጨዋታው ቀጥታ ወደ መለያ ምት አምርቷል።በዚህም ናይጄሪያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የነሐስ ሜዳሊያም አግኝታለች።

ግብጽ አራተኛ በመሆን ጨርሳለች።

በጨዋታው ናይጄሪያ የግብ እድል በመፍጠር፣ ግብጽ በኳስ ቁጥጥር የተሻሉ ነበሩ።

ናይጄሪያ ሶስት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አንስታለች።

ግብጽ ውድድሩን ሰባት ጊዜ በማሸነፍ ስኬታማዋ ሀገር ናት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም