የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከአዳማ ከተማ ጋር አቻ ተለያየ - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከአዳማ ከተማ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ- ግብር ሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መስፍን ታፈሰ ለሲዳማ ቡና ግቦቹን አስቆጥሯል።
አቡበከር ሳኒ እና ሙጂብ ቃሲም ለአዳማ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 30 ከፍ አድርጓል። ከተከታዩ ነገሌ አርሲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማስፋት እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
አዳማ ከተማ በ23 ነጥብ 7ኛ ደረጃን ይዟል።
ጨዋታውን ተከትሎ የ15ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
የ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።