ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ቼልሲ ድል ሲቀናው ሊቨርፑል ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማምሻውን አምስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቼልሲ ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ጆአኦ ፔድሮ በጨዋታ እና ኮል ፓልመር በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ34 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ብሬንትፎርድ በ33 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሊቨርፑል ከበርንሌይ አንድ አቻ ተለያይቷል። 

በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍሎሪያን ዊትዝ ለሊቨርፑል፣ ማርከስ ኤድዋርድስ ለበርንሌይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሊቨርፑል በጨዋታው ላይ ያገኘውን የፍጹም  ቅጣት ምት አማካዩ ዶምኒክ ስቦዝላይ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ሊቨርፑል በ36 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ሲይዝ በርንሌይ በ14 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በሌሎች መርሃ ግብሮች ሰንደርላንድ ክሪስታል ፓላስን ፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፈዋል።

ሊድስ ዩናይትድ ፉልሃምን 1 ለ 0 ረቷል።

በአሁኑ ሰዓት የሊጉ መሪ አርሰናል ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ጨዋታውን እያደረገ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም