ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከስድስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15 ሳምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን 4 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።


 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አምበሉ አቤል ያለው በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥርሀብታሙ ጉልላት እና ፍጹም ጥላሁን ደግሞ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የድሬዳዋ ከተማው አማካይ ሄኖክ ሀሰን 22ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። ይህም በጨዋታው ላይ ተጽእኖ አሳድሯል።

ከስድስት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ በ22 ነጥብ ደረጃውን 10 ወደ 7 ከፍ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱም ስድስተኛ ድሉን አሳክቷል።


 

በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ 18 ነጥብ ከነበረበት 12 ደረጃ ወደ 13 ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም