ኢትዮጵያ ቡና እና ሐዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ቡና እና ሐዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ሐዋሳ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ናይጄሪያዊው ዲቫይን ዋቹኩዋ በ38ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ኢትዮጵያ ቡና መሪ ሆኗል።
ጌታነህ ከበደ በ93ኛው ደቂቃ ለሐዋሳ ከተማ የአቻነቷን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና በ19 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
ሐዋሳ ከተማ በ25 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ ማድረግ ችሏል።