ቀጥታ፡

መቻል ወደ ድል ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15 ሳምንት መርሐ-ግብር መቻል አርባ ምንጭ ከተማን 2 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ 68ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት እና ዩጋንዳዊው ቻርልስ ሙሲጌ 91ኛው ደቂቃ በጨዋታ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 


 

ከሦስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው መቻል 23 ነጥብ ደረጃውን ከሰባተኛ ወደ ስድስተኛ ከፍ አድርጓል።

በሊጉም ስድስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባ ምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ በደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።

አርባ ምንጭ ከተማ በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ብቸኛው ክለብ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም