ቀጥታ፡

የከተራና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)የከተራና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

በዚህም መሠረት በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር በመቀናጀት ዝግጅት አጠናቆ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ኃይል በማሰማራት ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

ሕብረተሰቡም ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሲመለከት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በማድረስ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንም መልካም ምኞቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም