የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፦ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀና ፍፁም ባማረ መልኩ በሁሉም ስፍራዎች እንዲከበር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይቱም አጠቃላይ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ለመመልከት መቻሉን ተናግረዋል።
ከንቲባዋ የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የሚታደሙበትና በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ፣ እንደ ሌሎች ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ሁሉ የጥምቀት በዓልም በታላቅ ድምቀትና በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።