ሀዲያ ሆሳዕና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ሀዲያ ሆሳዕና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ጥር 8 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ምድረገነት ሽሬን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤልያስ አሕመድ እና ሱራፌል ተመስገን በጨዋታ፣ ብሩክ በየነ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ተካልኝ ደጀኔ ለምድረገነት ሽሬ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሀዲያ ሆሳዕና በ20 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል።
በሊጉ አምስተኛ ድሉንም አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ምድረገነት ሽሬ በ17 ነጥብ ከነበረበት 13ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ዝቅ ብሏል።