ቀጥታ፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታዋቂው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

ለአርቲስት ነጻነት ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና አድናቂዎች በሙሉ መጽናናትን  ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም