በዘርፉ በተደረጉ ማሻሻያዎች የኔትወርክ ተደራሽነት እና የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል - ኢዜአ አማርኛ
በዘርፉ በተደረጉ ማሻሻያዎች የኔትወርክ ተደራሽነት እና የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች አዳዲስ ኦፕሬተሮችን ወደ ስራ ከማስገባት ጀምሮ የኔትወርክ ተደራሽነት እና የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል ሲሉ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ (ኢንጅነር) ገለጹ፡፡
ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የሚያስችል ተቋማዊ አሰራርን መከተል ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።
ለዚህም በዘርፉ የሚሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ መስጠት፣ መከታተልና መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ (ኢንጅነር) ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ዘርፉ በራሱ እድገት እንዲያስመዘግብ ከማድረግ ባለፈ ለሌሎች ዘርፎች እድገት አስቻይ በመሆኑ በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።
አሁን ላይ በዘርፉ የተደረጉ ማሻሻያዎች አዳዲስ ኦፕሬተሮችን ወደ ስራ ከማስገባት ጀምሮ የኔትወርክ ተደራሽነት እና የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስታውቀዋል።
ይህ ዘርፍ በራሱ ከሚያስመዘግበው ውጤት ባለፈ ለሌሎች ዘርፎች አስቻይ በመሆኑ በዘርፉ ላይ የሚሰራው ስራ ወሳኝ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በተለይ ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለፋይናንስ ተደራሽነት፣ ቅልጥፍና እና ዘመናዊ አገልግሎት እየሰጠው ያለው አገልግሎት ተጠቃሽ ነው ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።