ቀጥታ፡

ባህር ዳር ከተማ እና መቀሌ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና መቀሌ 70 እንደርታ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። 

ጨዋታው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል።

ባህር ዳር ከተማ በ20 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።


 

መቀሌ 70 እንደርታ በ13 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ዛሬ በተደረገ የ15ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም