ቀጥታ፡

የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል በተሰናዳው እና ስድስት የሀገራችንን የፋይናንስ እና የገቢ ሥርዓት በመምራት ላይ ያሉ ዐበይት ተቋማት አፈፃፀም በሚገመግሙበት እና ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚኖራቸውን ስትራቴጂያዊ የቅድሚያ ምልከታ በሚያደርጉበት ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዋል።


 

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት በፋይናንስ አካታችነት ተጨባጭ እድገት ያስገኙ እና ሰፊ መዳረሻ ያላቸው የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርሞች አካሂዳለች።


 

ከገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት እስከ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃፀሞች እና የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ድረስ የእነዚህ አምስት አመታት ክንዋኔ በፋይናንስ ዘርፉ ተወዳዳሪነትን በሚያሳድጉ በመንግሥት ቆራጥ እና ስኬታማ ተግባራት የሚገለጥ ነው።

#PMOEthiopia

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም