ቀጥታ፡

"ሰላምን ማጽናት፤ ፀጋን ለማልማት" በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ትብብር የተዘጋጀው የፓናል ውይይት "ሰላምን ማጽናት፤ ፀጋን ለማልማት" በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው ።


 

በመድረኩ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቴ አለነ ፣ እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ሀገራዊ ምክክር እና የሰላም ግንባታ፣ በክልሉ የተከናወኑ የሰላምና ፀጥታ ስራዎችና እመርታዎችን በተመለከተ ጹሁፍ ቀርቦ ወይይት ይደረጋል ።

በተጨማሪም የአማራ ክልል የመልማት ተስፋዎች፣ የህዝብ ተጠቃሚነት ፣ የክልሉ ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም