ቀጥታ፡

የአይሾው ስፒድ የኢትዮጵያ ቆይታ በመላው ዓለም የሚሊዮኖች ዓይኖች አዲስ አበባ ላይ እንዲሆን አድርጓል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፦ ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ በኢትዮጵያ ያደረገው ጉብኝት በመላው ዓለም የሚሊዮኖችን ዓይን ወደ አዲስ አበባ የሳበ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ጉብኝቱ ከተማችን ያላትን የቆየና የከበረ የእንግዳ ተቀባይነት ባህልና የከተማችንን ፅዳትና ውበት ለዓለም የገለጠ ስኬታማ መርሐ ግብር ነበር ሲሉም ከንቲባዋ ብለዋል፡፡


 

የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል ያሉት ከንቲባዋ ወደ ፊትም ብዙዎችን ወደ ሀገራችን እንደሚስብ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሁነቱ እስከ አሁንም መነጋገሪያነቱ መቀጠሉን ገልጸው መርሐ ግብሩን ላስተባበሩ ሀገር ወዳድና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች፣ ለፌደራልና ለአዲስ አበባ መንግስታዊና የግል ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡


 

በተለይም የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ ይሳቃል ኢንተርቴይመንትና ሌሎች ባላድርሻ አካላት ላሳዩት ቅንጅት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም