በካራባኦ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አርሰናል ቼልሲን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በካራባኦ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አርሰናል ቼልሲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2018 (ኢዜአ)፦ በካራባኦ ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር አርሰናል ቼልሲን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቤን ዋይት፣ ቪክቶር ዮኮሬሽ እና ማርቲን ዙቢሜንዲ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አሊሃንድሮ ጋርናቼ የቼልሲን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አርሰናል በጨዋታው ላይ ተጨማሪ ግቦችን የማስቆጠር እድሎች አግኝቶ አልተጠቀመበትም።
የቼልሲው አዲስ አሰልጣኝ ሊያም ሮሲናየር በመጀመሪያ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግደዋል።
የአርሰናሉ አጥቂ ቪክቶር ዮኮሬሽ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
ትናንት በካራባኦ ዋንጫ በተካሄደው ሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል።
የመልስ ጨዋታው ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይደረጋል።