ቀጥታ፡

አዘጋጇ ሞሮኮ ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ሞሮኮ ናይጄሪያን በመለያ ምት አሸንፋለች።

ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግብ ባለመቆጠሩ 30 ደቂቃ ተጨምሯል።

በ120 ደቂቃ ጨዋታው ያለ ግብ አቻ በመጠናቀቁ ወደ መለያ አምርቷል።

በዚህም ሞሮኮ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፋለች።

በጨዋታው ላይ ሞሮኮ አንጻራዊ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች።

አዘጋጇ ሞሮኮ በፍጻሜው ከሴኔጋል እሁድ ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጨዋታዋን ታደርጋለች።

ሴኔጋል ዛሬ በተደረገ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፏ ይታወቃል።

የግማሽ ፍጻሜ ተሸናፊዎቹ ግብጽ እና ናይጄሪያ ቅዳሜ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም