ሴኔጋል ግብጽን በማሸነፍ ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈች - ኢዜአ አማርኛ
ሴኔጋል ግብጽን በማሸነፍ ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ሴኔጋል ግብጽን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
ማምሻውን በታንጀር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሳዲዮ ማኔ በ78ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ማኔ በውድድሩ ላይ ያስቆጠረውን ግብ ብዛት ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል።
በጨዋታው ሴኔጋል ከፍተኛ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች።
ግብጽ የጥልቀት መከላከል እና የመልሶ ማጥቃት የአጨዋወት ስልት ውጤታማ አልሆነም።
ውጤቱን ተከትሎ የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ሴኔጋል ለፍጻሜ አልፋለች።
በፍጻሜው ከናይጄሪያ እና ሞሮኮ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
ናይጄሪያ እና ሞሮኮ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ምሽት አምስት ላይ በፕሪንስ ሙላይ ስታዲየም ያደርጋሉ።